Discover Endashaw's journey through shared moments, insights, and progress
****** ለምን መጀመር ከበደክ/ሽ***** ታውቃለ ከአንት ህልም መሳካት ጀርባ ብዙ እንባቸው የሚታበስ ሰዎች እንዳሉ። እና ምን ትጠብቃለ ወንድሜ እህቴ በዚህ ዓለም ማንም perfect አይደለምም ሚሆንም የለምም ስለዚህ ለምን ነገሮች perfect እስኪሆኑ ጥጠብቃላችሁ ጀምር ከዛ የሆነ ቀን እንዲህ በለኝ/በይኝትዝ ይልካል የዛኔ ጀምር ስትለኝ ጀምሬ እዚህ ደርሻለው በለኝ እኔ አምንብካለው አዎ አምንብሻለው ችግሩ አንተ ታምንበታለ ወይ ነው? አንቺ ታምኝበታለሽ ወይ ነው? ባንተ ላይ ባንቺ ላይ እወዳቸዋለሁ
ታላቅ ሀገራዊ ገንዘብ ማሰባሰቢያ አረገዊያንን እና አእምሮ ህሙማንን ከወደቁበት እያነሳ የሚጦረው ታላቁ የበጎ አድራጎት ድርጅት መቄዶንያ እያሰራ ያለውን ታላቁን ህንፃ ለfinishing ስራ የሚያስፈልገውን ከ 4,000,000,000 ብር በላይ በተወዳጁ ሰይፉ ፋንታውን የyoutube channel ከዛሬ ጀምሮ በlive ገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ይደረጋን እና እናንተም በምስሉ ላይ በሚገኙ የገቢ ማሰባሰቢያ አማራጮች የዚህ ታላቅ መርሀግብር ላይ የታሪክ ተካፋይ ይሁኑ
***************** PROCESSE *************ከግብፅ ወደ ከነዓን ነገሬን ከጥያቄ ልጀምር 🤔 ለምን እስራኤላውያን ከግብፅ ወደ ከነዓን ለመግባት 40 ዓመት ፈጀባቸው?ሂደት ሚባል ነገር ታውቃላችሁ? ሁሉም ነገር ሂደት አለው ጊዜ አለው ምክንያትም አለው ። ብዙዎቻችን እኔንም ጨምሮ ይሄን ባለማወቃችን እግዚአብሔር እናማርራለን እግዚአብሔር የሚያውቀው እኛ ምናውቅ የሚመስለን ነገር ግን የማናውቀው ብዙ ነገር አለ። ብዙዎቻችን ከእግዚአብሔር እንዲሰጠን ፣ እንዲደረግልን የምንፈልገው ነገር አለ። ነገር ግን እኛ በፈለግነው ጊዜ እና ሰዓት ⌚ ካልሆነ አምላካችን የተወን እና የረሳን ይመስለናል ግን እውነታው ይሄ ነው ለሁሉም እግዚአብሔር ጊዜ አለው። ወደ እስራኤላውያን ጉዙ ልመለስ እና ነገሩን ላስረዳችሁ እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት ለብዙ አመታት ተገዝተዋል እና አሁን ላይ በባርነት መንፈስ ነው ያሉት እና እግዚአብሔር በ4ቀን በዚህ መንፈሳቸው ከነዓንን ቢወርሱ ምን የሚፈጠር ይመስላችዋል መልሱን ለናንተ ተውኩት።ሌላው እግዚአብሔርን ያወቁት (ከዛ በፊት አያውቁትም ማለቴ አይደለም) በ40 ዓመት ጉዛቸው ነበር መጋቢነቱን ፣ ይቅርባይነቱን፣ ግርማውን፣ ቁጣውን፣አሸናፊነቱን፣ተአምራዊነቱን ብቻ ይሄንን አምላካቸውን ሳያቁት ከንዓንን ቢወርሱ ምን ይፈጠር ይመስላችዋል?ነገሩን ሳሳጥረው ከባርነት መንፈስ መላቀቅ ነበረባቸው፤ ለከነዓን ምድር ብቁ ሆነው መሰራት ነበረባቸው ይሄ ሂደት ይባላል። ወንድሜ እህቴ አምላክ አይደለም የነገርሹን ያሳብሹን ያቃል ግን ጊዜ አለው። ለተየቅሹ ኃላፊነት ብቁ መሆን አለብሽ ታገሽ እስራኤላውያን 40 ዓመት ቢፈጅባቸውም ከነዓን ገብተዋል የዝግጅት ጊዜ ቢቆይም እግዚአብሔር ህልምክን ያሳካዋል ተስፋ አትቁረጥ ይልቅ በዝግጅት ጊዜ ሊያስተምር የፈለገውን ነገር በደንብ ተማር።እግዚአብሔር ለሁሉም ጊዜ አለው። ሀሳቡ የተወሰደው ከ A Live podcast ከማዕዛ ፋንታው አንደበት ነው።
ሰው አያልቅስብ እንዳታለቅስሰው አያልቅስብ ዘር እንዳይጠፋ፣እድሜክ እንዳያጥር ሁለቱንም አለም እንዳታጣ በስጋህም የወዲያኛውንም ያለቀሰው ወገንህን እንባውን አብስ በቁም እንዳትነድ እንባ! እሳት🔥 ነው ።እንባ! መዶሻ 🔨 ነው።እንባ ሰይፍ 🤺 ነው።አባቴ ልጅ ሆኜ እንባ የሰበረው አይጠገንም፣አያንሰራራም ፤ እንባ የጣለው ትንሣኤ የለውም፤ ይሉ ነበር አይገባኝም ነበር።ውኃ አይደል እንዴ ምን ማለታቸው ነው እንዴት ነው የሚሰብረው 🤔 ኡ ኡ ኡይ እንባ! አረ ቃላት የለም እንባ! የሚያመጣው ፍዳ፤ እንባ የሚያመጣው እሳት አረ ቃላት የለውም አይገለጥም። ሰው አታስለቅስከስብከት የተወሰደ
************* ብር ወይስ ጠላት ***********ይህ በምስል ላይ ምትመለከተው ላንተ ብር ነው ወይስ ጠላት?ምንድነው የምታወራው?የማወራውም ስለ ገንዘብ አጠቃቀም ነው።እና ምን አገናኘው ገንዘብ አጠቃቀምና ጠላትነት?ጥሩ ጥያቄ ነው ምን መሰለ ይሄን በምስሉ ላይ ምታየውን እየተጠቀምክበት ከሆነ ገንዘብ/ብር ነው ላንተ ።ካልሆነስ?ካልሆነማ ጠላት ነውእንዴት?ጥሩ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እንዲ ብሎ አስተምሯል'አስቀድማችሁ የእግዚአብሔር ጽድቁን እና መንግስቱን ፈልጉ ሌላው ሁሉ ይጨመርላችኋል' ማቴዎስ 6:33 ይላል።ምን አገናኘው?በጣም ጥሩ ኪስክ ውስጥ ወይም ዋሌትውስጥ ባለው ብር ምን እያረክበትነው ለተቸገሩ እያበላህበት ነው፣ ለተጠሙ እያጠጣህበት ነው፣ ለታረዙ መንገድ ዳር ላሉ ህጻናት እያለበስክበት ነው፣ የታመመ ወዳጅህን እየረዳህበት ነው ይህን እያረክበት ከሆነ በብርክ እነጸደክበት ነውና ላንተ ጠላት ሳይሆን ብር ነው።ነገር ግንአየሰከርክበት ከሆነ ፣ በገንዘብ ሰው አያስገደልክበት ፣ ደሀ እየበደልክበት፣ የሴት እህቶችን ህይወት እያመሰቃቀልክበት ከሆነ እመነኝ ላንተ ብር ሳይሆን ጠላትክ ነው ምክንያቱም የእግዚአብሔርን መንግስትና ጽድቁን እያሳጣክ ነውና ይሄ እህቴ ላንቺም ነው።
ገና የጌታችን የመድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እውነት ነው የጌታ ልደት ነው ግን ጥያቄው እንዴት ልታከብረው እንዴት ልታከብሪው አሰብክ አሰብሽ ግን ከዛ በፊት ነገ በጣም የምቶጃት በጣም የምቶደው የጓደኛ ልደት ቢሆን ምን ነበር ምታረገው? ምታረጊው? እርግጠኛነኝ ምን ለብሰ እንደምቴድ ምን ስጦታ ይዘሽላት እንደምቴጅ ግራ ገብቶሽ ጨንቆሽ ነበር ሚሆነው ለምን ቢባል በልደቷ ቀን አሷን ለማስደሰት እና ጓደኝነትክን ለማሳየት እና ለጓደኛሽ ይሄን ያክል ከተጨነቅሽ ለፈጣሪሽለአምላክሽ ፍቅሩን ከዙፋኑ ወርዶ በበረት ተወልዶ በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ ስላንቺ ሲል 6666 ጊዜ በጅራፍ ተገርፎ ይሄ ሁሉ አልበቃ ብሎት ፍቅሩን በመስቀል ላይ ለገለጸልሽ እስከሞት ለወደደሽ አባትሽማ ምን ያህል ነበር መጨነቅ የነበረብን እውነታው ግን ሌላ ነው ።ስለ አኛ ብሎ መራራ አሞት ጠጣ እኛ ግን በልደቱ ቀን ቢራ እና ውስኪ እንጠጣለን።ስለ እኛ ብሎ በጥፊ ተመታ አኛ ግን በልደቱ ቀን ሰክረን እንጣላለን።ስለ እኛ ኃጥያት እሱ የሞት ዋጋ ከፈለልን አኛ ግን በልደቱ ቀን በኃጥያት እንወድቃለን።ምን እናርግ እና?ስጦታ እንስጠው ለማ?ለባለ ልደቱ ነዋእንዴት?በጣም ጥሩ እንዲ ይላል የእግዚአብሔር ቃል'በእኔ በሚያምኑ ለታናናሾቻቹ ያደረጋቹት ለእኔ እንዳደረጋቹ ይቆጠራል' እና ነገ ቤተክርስቲያን ሂድ ሂጂ እግዚአብሔርን ከምስኪኖቹ ጋር ታገኙታላቹሁ ለእነሱ ያደረጋችሁት ለእሱ እንዳደረጋችሁ ይቆጠርላቸዋል። በተረፈ ነገ ብርሃን የበራልን ቀን ነው ጨለማ ህይወታችሁ ይበራ ዘንድ ንሰሐ ግቡ በተረፈ መልካም በአል።
You've seen all moments
Start sharing your language learning journey and connect with partners worldwide.